Disclaimer: The material in this print-out relates to the law as it applies in the state of Victoria. It is intended as a general guide only. Readers should not act on the basis of any material in this print-out without getting legal advice about their own particular situations. Victoria Legal Aid disclaims any liability howsoever caused to any person in respect of any action taken in reliance on the contents of the publication.

We help Victorians with their legal problems and represent those who need it most. Find legal answers, chat with us online, or call us. You can speak to us in English or ask for an interpreter. You can also find more legal information at www.legalaid.vic.gov.au

Read about our reduced hours over the holiday period.
Contacting us over the holidays.

Amharic/አማርኛ

Amharic/አማርኛ – ህጋዊ በሆኑ ችግሮች ላይ እንዴት እንደምንረዳ

ህጋዊ በሆኑ ችግሮች ላይ እንዴት እንደምንረዳ

ይህ መረጃ የወጣው በ Wurundjeri መሬት ላይ ነው።

ይህ መረጃ ከጥር/ጃንዋሪ 2022 ዓ.ም ጀምሮ ትክክል ነው።

ሕጋዊ ችግሮች የጭንቀት፣ የመረበሽ፣ የማዘን ወይም የመናደድ ስሜትን ሊፈጥርብዎ ይችላል። በሚያነጋግሩን ጊዜ እንዚህ ስሜቶች ሊኖርዎት እንደሚችሉ እንገነዘባለን። ሕጋዊ ችግሮች ላይ ልንረዳዎት እንችላለን።

ስለ ሕጋዊ ችግር እንዴት ሊነግሩን እንደሚችሉ

ሰለ ሕጋዊ ችግርዎ የሚነግሩን የሚችሉበት ሶስት መንገዶች አሉ። እነሱም:

  • ለህጋዊ እርዳታ በስልክ Legal Help 1300 792 387
  • ዌብቻታችንን (webchat) በመጠቀም በመስመር ላይ ይጻፉልን።
  • ከቢሮአችን አንዱን ይጎብኙ።

ለመዘጋጀት፣ ሕጋዊ ችግር ነው የሚሉትን ማንኛውንም መረጃ ያግኙ። የጽሑፍ መረጃዎች ጥሩ ናቸው ወይም ደብዳቤ ወይም ክፍርድ ቤት ኢሜል፣ ዳኛ ወይም ፖሊስ።

  1. ለሕግ እርዳታ Legal Help ይደውሉ

ለሕግ እርዳታ Legal Help በስልክ ቁጥር 1300 792 387 ይደውሉ።

የሕግ እርዳታ Legal Help ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከጠዋቱ 8 ሰዓት እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት ክፍት ነው።

የስልክ ክፍያው እንደመደበኛ የሃገር ውስጥ ጥሪ ነው።

ማንኛውም ሰው ለሕግ እርዳታ Legal Help መደወል ይችላል።

ለሕግ እርዳታ Legal Help ከደወሉ፣ መጠበቅ ሊኖርብዎት ይችላል። የሚችሉ ከሆነ በጠዋት ይደውሉ።

ዌብቻታችንን (webchat) መጠቀም ሊፈጥን ይችላል።

ሠራተኞቻችን በርካታ ቋንቋዎችን ይናገራሉ። ቋንቋዎን መናገር ካልቻልን፣ በሚደውሉበት ወቅት አስተርጓሚ እናዘጋጃለን።

ቁንቋዎን መናገር የምንችል መሆኑን ይወቁ (speak your language.)

ሌላ ሰው ሊደውልልኝ ይችላል?

አዎን። ሠራተኛ ወይም የሚያምኑት ድጋፍ የሚያደርግልዎ ሰው ሊደውልልን ይችላል። በሚደውሉ ጊዜ ከሠራተኛው ወይም ከድጋፍ ሰጪው ሰው ጋር ቢሆኑ ጥሩ ነው። ሠራተኞች በስልክ ማውጫው ላይ ያሉትን መመሪያዎች መከተል አለባቸው።

የሃገር አቀፉን የማስተላለፊያ አገልግሎት (National Relay Service) መጠቀም እችላለሁ?

አዎን።የተለያዩ አማራጮች አሉ:

  • TTY: በስልክ 133 677 ይደውሉ እና በዚህ ስልክ 1300 792 387ይደውሉ
  • ይናገሩ እና ያዳምጡ: በስልክ ቁጥር 1300 555 727 ከዚያ በስልክ ቁጥር 1300 792 387 ይደውሉ
  • የድረገጽ ማስተላለፊያ: ወደ nrschat.nrscall.gov.au ይሂዱ ከዚያም በስልክ ቁጥር 1300 792 387 ይደውሉ
  • የአጭር መልእክት ማስተላለፊያ (SMS): በእዚህ ቁጥር ይላኩ 0423 677 767
  • የቪዲዮ ማስተላለፊያ: ስካይፕ ወይም የሃገር አቀፉን የማስተላለፊያ አገልግሎት አፕ ይጠቀሙ
  • የሃገር አቀፉን የማስተላለፊያ አገልግሎት ከመጠቀምዎ በፊት መመዝገብ አለብዎት።

2. በዌብቻት ላይ ይጻፉልን webchat (በእንግሊዝኛ ብቻ)

ዌብቻታችንን (webchat) ይጠቀሙ፣ ለሠራተኖቻችን የሕግ ችግርዎን ለማስተላለፍ Legal Help Chatን ይጠቀሙ። ሠራተኞቻችን መልስ ይሰጡዎታል። ተጨማሪ እርዳታ ከፈለጉ ለሕግ እርዳታ እንዲደውሉ ሊነግሩዎት ይችላሉ።

3. ይጎብኙን

ቢሮአችንን ሊጎበኙ ይችላሉ፡ በሜልበርን እና በቪክቶሪያ በተለያዩ ቦታዎች ቢሮዎች አሉን። ቢሮዎቻቻን የት እንደአሉ ይፈልጉ (where we have offices.)

ከጠበቃ ጋር መነጋገር ከፈለጉ ቀጠሮ መያዝ አለብዎት።

ቢሮዎቻችን የተሽከርካሪ ወንበሮች መውጫዎች አሏቸው በእንሰሳት ላይም ክልከላ የለም።

በሚያነጋግሩን ጊዜ ምን ይፈጠራል

ጥያቄዎች እንጠይቅዎታለን። ይህም ምን አይነት እርዳታዎች ልናደርግልዎት እንደምንችል ይረዳናል።

የሚነግሩን ሁሉ በምስጢር ይያዛል። የነገሩንን ሁሉ እርስዎ ካልፈቀዱልን በስተቀር ለማንም አንናገርም።

በብዙ የሕግ ችግሮች መርዳት እንችላለን። ጥያቄዎን መመለስ ካልቻልን፣ መልስ ሊሰጡዎች ወደሚችሉድርጅቶች የመገናኛ ዝርዝራቸውን እንሰጥዎታለን። ይህም የማህበረሰብ የሕግ ማእክል ወይም የግል ጠበቃ ሊሆን ይችላል።

እንዴት እንደምንረዳ

የሕግ መረጃዎች እና ምክር

ስለሕግ እና ስለ አለዎት ምርጫዎች እንነግርዎታለን።

በተጨማሪም በሚከተሉት ልንረዳዎት እንችላለን:

  • መረጃ እንልክልዎታለን
  • ከፍርድ ቤት በፊት እናነጋግርዎታለን
  • ከሌሎች አገልግሎቶች እና ድጋፎች ጋር እናገናኝዎታልን
  • ደብዳቤዎች መጻፍ እንጽፍልዎታለን
  • ፍርድ ቤት እንቆምልዎታለን።

ይህም የሚከተሉት ይወስኑታል:

  • ያለዎትን ሕጋዊ ችግር
  • ምን ያህል ገንዘብ እንዳለዎት።

ተጨማሪ እርዳታ ልናደርግልዎት እንችል ይሆናል:

  • በእንግሊዝኛ የመናገር ችግር ካለብዎት
  • አካል ጉዳተኛ ከሆኑ ወይም የአእምሮ ጤና ችግር ካለብዎት
  • አቦሪጅናል እና/ወይም ቶሬስ ስትሬት አይላንደር ከሆኑ።

ከኛ ጋር እንዲገናኙ ድጋፍ ማዘጋጀት እንችላለን፣ እንደ አስተርጓሚዎች ወይም የሃገር አቀፍ የማስተላለፊያ አገልግሎት።

ይረዳኛል በሚሉት መንገድ ከእርስዎ ጋር ግንኙነት ማደረግ እንችላለን።

መረጃ በምን ዓይነት መንገድ እንድንሰጥዎ እንደሚፈልጉ ይንገሩን።

ተረኛ ጠበቃች (Duty lawyers)

ትረኛ ጠበቆቻችን (duty lawyers) በመላ ቪክቶሪያ ፍርድ ቤቶች ይሠራሉ። በአንድ አንድ የሕግ ችግሮች ይረዳሉ። ፍርድ ቤት የሚሄዱ ከሆነ እና ጠበቃ ከሌለዎት፣ ፍርድ ቤቱን ከተረኛ ጠበቃ duty lawyer ጋር መነጋገር ይችሉ እንደሆነ ይጠይቁ። በተጨማሪም ሊረዱዎት የሚችሉ ሌሎች አገልግሎቶች እንዳሉ መጠየቅ ይችላሉ።

ፖሊስ ሕግ ተላልፈዋል ብሎዎት ወደ ማጅስትሬት ፍርድ ቤት የሚሄዱ ከሆነ፣ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄድዎ በፊት ተረኛ ጠበቃ ለማነጋገር ይችሉ ይሆናል። ስለ Help Before Court service ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ።

ወደ ቤተሰብ ፍርድ ቤቶች የሚሄዱ ከሆነ፣ ፍርድ ቤት ከመሄድዎ በፊት Family and Advocacy Support Services የሚልውን አገልግሎት መጠየቅ ይችሉ ይሆናል።

ሌላ አገልግሎት

ሰለ ሕጋዊ ችግር ሌላ ድጋፍ ማድረግ እንችላለን።

Independent Mental Health Advocacyየተሰኘው ድርጅት አስፈላጊ የአእምሮ ህክምና የሚያደርጉ ከሆነ ሊረዱዎት ይችላሉ።

Independent Family Advocacy and Support የተሰኘው ድርጅት ወላጆችን እና አሳዳጊዎችን የልጅ ጥበቃ ስርአትን በተመለከተ በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ሊደግፉዎት ይችላሉ።

እርስዎ እና የትዳር ጓደኛዎ የሚለያዩ ከሆነ Family Dispute Resolution Service የተሰኘው አገልግሎት ስምምነቶች ላይ እንድትደርሱ ይደግፋል። ለምስሌ፣ ልጆቹን ማን እንደሚንከባከብ።

ስላለዎት ሕጋዊ ችግር ተጨማሪ መረጃ ያግኙ

ድረገጻችን website በበርካታና በተለያዩ የሕግ ችግሮች ላይ መረጃ አለው።

በደረገጹ ላይ ዙም በማድረግ ወይም ስክሪን ሪደር (screen reader) ይጠቀሙ።

ሰለ ኢዚ ሪድ (easy read) ወይም ቋንቋዬ መረጃ አለዎት?

በአንድ አንድ የሕግ ጉዳዮች ላይ በተለያዩ ቋንቋዎች እና በኢዚ ሪድ (easy read) የነፃ መጽሔቶች አሉን።

መጽሔቶቻችንን በካታሎግ ገጻችን catalogue page ላይ ያገኟቸዋል።

ጽሑፎርቻንን ለማንበብ ስክሪን ሪደር (screen reader) መጠቀም ይችላሉ።

እውቅና መስጠት

የእኛ Shared Experience and Support እና Speaking from Experience ቡድኖች ይህንን ገጽ ለማጻፍ እረድተዋል።

Updated

Legal Help Chat